ካይዘን ምንድን ነዉ

ካይዘንየሚለውቃልየተመሰረተው’’Kai ‘’እና ‘’Zen’’ ከተባሉየጃፓንኛቃላትሲሆን’’Kai ‘’ማለትለውጥ(Change)ማለትሲሆን‘’ Zen ‘’ደግሞ የተሻለ ማለትነው፡፡ከዚህ አንጻርም ካይዘን ማለት በቀጣይነት ላይ የተመሰረተ የተሻለለውጥ ማለት ነው፡፡

የካይዘን አመራር ፍልስፍና ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው የተሻለ ለውጥ ማምጣት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ፍልስፍናው ከሁሉም በላይ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ነው፡፡ነባራዊ ሁኔታን በመረዳት አመራሩንና ሰራተኛውን አሳታፊ በማድረግ ለለውጥ፣ ለጥራትና ለምርታማነት ንቅናቄ ያነሳሳል፡፡ዋና የለውጥ ተዋናይ አድርጎ የሚወስደው የሰው ኃይሉን በተለይም ፈጻሚውን ሲሆን ሠራተኛው በካይዘን አመራር ፍልስፍና በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ቀጣይነት ያለውየተሻለ የለውጥ ሥራን በንቃት ተሳታፊ እንዲሆን ማስቻል ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡

ስለካይዘን ለመረዳት በቅድሚያ በጃፓን በሂደት የዳበሩ የስራ አመራር እንዲሁም የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ዘዴዎችን ከመሰረቱ መገንዘብን ይጠይቃል፡፡ጃፓን ኢንዱስትሪዎቿን ያሳደገችው በአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ልማት ላይ ትኩረት ሰጥታበመስራቷ ሲሆን ለዚህም የካይዘን ፍልስፍና በእጅጉ ጠቅሟታል፡፡ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጃፓን ለዓለም ገበያ ታቀርብ የነበረውምርቶችጥራት አሜሪካና አውሮፓ ከሚያመርቷቸው ምርቶች ጋር ሲነጻጸር በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ በዓለም ገበያ ላይተወዳዳሪ መሆን አልቻለችም ነበር፡፡

ይህን ችግሯን ለመፍታት ከሌሎች ሀገሮች ለመማር ወሰነች፡፡በተለያዩ ሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁሮቿን ወደአውሮፓና አሜሪካ በመላክ የእነዚህን ሀገሮች አሰራርእና ቴክኖሎጂ በመቅሰምና በመቀመር ከራሷ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ማጣጣም ጀመረች፡፡ዜጎቿም ተግተው በመስራት የራሳቸውን የካይዘን አመራር ፍልስፍና በመቀመር በጥራትና ምርታማነት ላይ የተመሰረተፈጣን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ ልማት ያስመዘገበች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከበለጸጉ ግንባር ቀደምሀገራት አንዷለመሆን በቅታለች፡፡

ካይዘን ምርትና አገልግሎትን ተወዳዳሪና ዉጤታማ በማድረግ የጋራ ተልዕኮን ከማሳካት አካያ ከፍተኛና መካከለኛ አመራርን እንዲሁም ሠራተኞችን ያስተሳስራል፡፡በተጨማሪ ሰው በማንኛዉም ቦታ እና ጊዜ ለውጥና መሻሻልን አስቦ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ፣ፈጠራና አዲስ አስተሳሰብን የሚያበረታታ እንዲሁም ሰፊ የለውጥ፣የጥራትና የምርታማንት ንቅናቄን በመፍጠር ስኬታማ የሚያደርግ የአመራር ፍልስፍና ነው፡፡

ከዚህም የተነሳ ይህፍልስፍና ለሀገራችንልማት ተመራጭ ሆኗል፡፡የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐፕብሊክ ልማታዊ መንግስት በመሆኑ የካይዘን የአሳታፊነት ባህሪይ ለሀገሪቱ አመራር የበለጠ ተስማሚ ነዉ፡፡

Designed by: HR ICT Solutions PLC  © Ethiopian Kaizen Institute