የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት አመሰራረት

ይህ ፍልስፍና ወደ ሀገራችን የመጣው እ.ኤ.አበ2008 በግብጽና በቱንዚያ የተካሄደውን የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ውጤት ሪፖርት ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ተገንዝበው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ለጃፓን መንግስት ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ ነው፡፡ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ በኢትዮጵያና በጃፓን መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት የካይዘን የሙከራ ትግበራ ፕሮጀክት ተቀረጸ ፡፡

በጃፓን አለምአቀፍ ትብብር ኤጀንሲ(Japan International Cooperation Agency} ድጋፍ ከተላኩት የጃፓን አማካሪዎች ጋር በመሆንበአዲስ አበባና በ100 ኪሎሜትርዙሪያ የሚገኙ ሠላሳ ኩባንያዎች ተመርጠውከጥቅምት 2002 እስከ ግንቦት 2003 የሙከራትግበራ(Pilot Project)ተከናውኗል፡፡
በሙከራ ትግበራውም ማለፊያ ውጤት የተገኘ ከመሆኑም በላይየካይዘንን ተሸጋጋሪነትና ጠቀሜታአረጋግጧል፡፡ ሙከራውንየተገበሩ ኩባንያዎችም በአመራሩ እና በሠራተኞች ላይ የአመለካከት ለውጥ ያመጣላቸው ሲሆን የሚያመርቱት ምርትጥራት፣ዓይነትናብዛትም ጨምሯል፡፡በዚህም ካምፓኒዎቹም ሆኑ ሰራተኞች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በሙከራ ትግበራው በተገኘው አበረታች ውጤትም መንግስት የፍልስፍናውን ልማታዊ ሚና በመገንዘብና ለልማታዊ መንግስት አመራር ያለውን አመችነት በመረዳት የካይዘን ፍልስፍና የአመራራችን ፍልስፍና እንዲሆን ወስኗል፡፡

ሌሎች የአመራር ጥበቦችንና የለውጥ መሳሪያዎችን ከዚህ ፍልስፍና ጋር በማጣጣም መጠቀም እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
በቀጣይነት ፍልስፍናውን ማሸጋገር፣ማጣጣምና ማስረጽ የሚያስችል ሀገራዊ አቅም መፍጠርን መሰረት ያደረገ ኢንስቲትዩት በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 256\\2004 እንዲቋቋም ተደረገ::

Designed by: HR ICT Solutions PLC  © Ethiopian Kaizen Institute